በከተራ በዓል ላይ በደረሱ የኤሌክሪክ አደጋዎች 2 ወጣቶች ሞቱ።


ትላንት በአማራ ክልል በሰቆጣ እና በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ሸረሮ ከተሞች የከተራ በዓል በሚከበርበት ወቅት በደረሰ የኤሌክትሪክ አደጋ የ2 ወጣቶች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አሰታውቋል።
የሰቆጣ ከተማ ፖሊስ ፅህፈት ቤት በከተማው የከተራ በዓል በሚከበርበት ወቅት ታቦታቱን ከፀሃይ የሚከላከል ጥላ ከኤሌክትሪክ ጋር በመነካካቱ በተከሰተ የኤሌክትሪክ አደጋ የአንድ ወጣት ህይወት ወድያው አልፏል።
በሌሎች ጥላውን በመግፈፍ ላይ በነበሩ ስምንት ወጣቶች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።
የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ወጣቶች በሰቆጣ ተፈራ ሃይሉ መታሰቢያ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው።
በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረሊባኖስ ወረዳ ሸረሮ ከተማ ለጥምቀት በዓል ማድመቂያ ሰንደቅ ዓላማ ለመስቀል የሞከረ የ24 ዓመት ወጣት ህይወቱ ማለፉን የወረዳው ፖሊስ አስታውቋል።
ወጣቱ ፎቅ ላይ ሆኖ የወረወረው ገመድ 33 ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኅይል ማስተላለፊያ ገመድ ላይ በማረፉ በእርጥብ እንጨት ለማንሳት ሲሞክር በኤሌክትሪክ ሀይል ተገፍተሮ ሊወድቅ ችሏል።
ወጣቱ ወደ ሽረሮ ጤና ጣቢያ ቢወሰድም ከ30 ደቂቃ በኃላ ህይወቱ አልፏል። ~ ENA
0 Comments