#United States

የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ የአሜሪካ መንግሥት  ማሳሳቡ ተሰምቷል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ለመገናኛ ብዙኃን በላኩት መግለጫ፤ ትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ ዘረፋ፣ መደፈር፣ እና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደሚፈፀሙ ታማኝ ከሆኑ ሪፖርቶች ሰምቻለሁ ብለዋል።


ቃል አቀባዩ አያይዘውም “በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞችን የኤርትራ ወታደሮች በሃይል ወደ ኤርትራ እየመለሷቸው ስለመሆኑ ማስረጃ አለ” ብለዋል። Electronics

አሶሼትድ ፕሬስ ከትግራይ ክልል የወጡ የዐይን እማኞችን ጠቅሶ ባጠናቀረው ዘገባ፤ የኤርትራ ወታደሮች ዘረፋ እንደሚፈፅሙ፣ ቤት ለቤት እየተዟዟሩ ሰዎችን እንደሚገድሉ እና ልክ እንደ አካባቢው አስተዳዳሪ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ሃገር ከድተዋል ተብለው የሚታመኑትን የህወሓት አመራሮች ለመያዝ በሚያደርገው ውጊያ ውስጥ የኤርትራ ወታደሮች ተሳትፈዋል ያለው ዘገባው ፤ ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት የኤርትራ ወታደሮች መሳተፋቸውን ሙሉ ለሙሉ አስተባብሏል ብሏል። (ምንጭ:አሶሼትድ ፕሬስ፣ የአሜሪካ ድምፅ)