ሰበር መረጃ ‼️
ቆላ ተንቤን ላይ ተደብቆ የቆየው ዋናው የጁንታው ክፋይ እጅ እንዲሰጥ ቢጠየቅም አሻፈረኝ ብሎ በመከላከያ ላይ ጦርነት ከፍቶ ባለፉት አራት ቀናት ውጊያ ሲደረግ ነበር!

በመከላከያ በኩል የሰራዊቱ ምክትል ኢታማዦር ሹም የሆነው ጀግናው ሌቴናል ጀኔራል አበባው ከመቀሌ ወደ ግንባር በመሄድ ጦርነቱን መርተው ጁንታውን ሙሉ በሙሉ ደምስሰው ትናት ወደመቀሌ ተመልሰዋል።
በቆላ ተንቤን የመሸገው ጁንታ ላይ መከላከያ የወሰደው እርምጃ ለወሬ ነጋሪ የሚተርፍ እንደሌለ እርግጠኛ የሚያደርግ ነው ተብሏል።
በዚህ የጁንታው ክፋይ ውስጥ የነበረውን አንጻራዊ ጥንካሬ ሲታይ መሪው #ጌታቸው_አሰፋ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። ለማንኛውም መከላከያ በዚህ የጁንታው ክፋይ ውስጥ እነማን እንደነበሩ ለማወቅ እስካሁን ድረስ የሟቾችን አስክሬን እየፈተሸ ነው።

1 Comments
Ethiopian news
ReplyDelete