ሱፍ ለጤና የሚሰጠው ጠቀሜታ

 ሱፍ ለጤና የሚሰጠው ጠቀሜታ



ሰላም ውድ የሸገር 24 ሚዲያ አምድ ተከታታዮቻችን እነሆ ዛሬ እንደተለመደው አዳዲስ ይጠቅማሉ ያልናቸውን መረጃዎች ይዘን መተናል። ከቅባት እህል ከሚመደበው ሱፍ ምን የጤና ጠቀሜታ እናገኝ ይሆን?
የሱፍ ተክል ዓመቱን በሙሉ ልናገኘው የምንችለው እና በርካታ የጤና ጥቅሞችን ሊያስገኝልን የሚችል የቅባት እህል ነው።
ብዙዎቻችን በተለይ የሱፍ ፍትፍትን ለብቻውም ሆነ በተለምዶ በየአይነቱ በምንልው የምግብ ዝርዝር ላይ እንደ አይነት ጨምረን እንመገበዋለን።
Health and beauty category ይሁንና ሱፍ ከምናስበው በላይ በርካታ ጥቅሞችን ለሰውነታችን እንደሚያበረክትስ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን?
እኛም ታዲያ ሱፍ ለጤናችን ከሚያበረክታቸው እጅግ በርካታ ጠቀሜታዎች መካከል የተወሰኑትን ለማየት ወደድን፦
1ኛ. ካንሰርን ይከላከላል፣
ሱፍ ሴሊኒየም የተባለው ንጥረነገር መገኛ እንደመሆኑ መጠን የሰውነት ህዋስ (ሴል) ጉዳትን በመከላከል ለካንሰር እንዳንጋለጥ ያግዛል፣
2ኛ. ለአጥንት ጥንካሬ፣
ሱፍ ከካልሲየም ውጪ ለአጥንት ጥንካሬ ጠቃሚ የሆኑ ማዕድናትም መገኛ ነው።
ካልስየም፣ ማግንዚየም፣ ኮፐርን የመሳሰሉ ማዕድናትን በውስጡ በመያዙም ለአጥንታችን ጤንነት እና ጥንካሬ ተመራጭ ነው።
በተጨማሪም ሱፍ ቫይታሚን ኢ በውስጡ ስለሚገኝ ከአተነፋፈስ ጋር ለተያያዙ ህመሞች ፍቱንነቱ ይነገርለታል።
Health and beauty category 3ኛ. ጭንቀትን ያስወግዳል፣
በሱፍ ውስጥ የምናገኘው የማግኒዚየም ማዕድን የነርቭ ስርዓትን የማነቃቃት ባህሪ ስላለው በቀላሉ ለጨንቀት እንዲሁም ለከባድ የራስ ምታት እንዳንጋለጥ ያግዛል።
Health and beauty category

 4ኛ. ለንፁህ እና አንፀባራቂ ቆዳ፣
በሱፍ ውስጥ በበቂ መጠን የምናገኘው ቫይታሚን ኢ ፥ ዩ ቪ ሬይስ የተሰኘው እና በቆዳ ላይ ጉዳት የሚያደርሰውን የጨረር አይነት በመከላከል እንዲሁም ቆዳችንን በማሳመር ማራኪ ቆዳ እንዲኖረን ያስችላል።
በሰውነት ውስጥም ሆነ ውጪ የማቃጠል ስሜትን ለመግታት፣
በሰውነት ውስጥም ሆነ ውጪ የሚከሰትን የማቃጠል ስሜት ለመግታት፣ በመገጣጠሚያ አካላት ላይ የሚደርስ ህመምን ለማስቆም እና ለጨጓራ ህመም መፍትሄው አሁንም ሱፍን አዘውትሮ መመገብ ነው።

Health and beauty category 5ኛ. የልብ ህመምን ለመከላከል፣
በቀን ከግማሽ ኩባያ ያነሰ ሱፍን ከምግብ ገበታችን ዝርዝር ውስጥ በማካተት ጎጂ የኮሌስትሮል መጠንን ከደም ቧንቧችን ላይ እንዲወገድ በማድረግ የልባችን ጤንነት በእጅጉ እንዲጠበቅ ማድረግ እንችላለን።

Computing Category

Post a Comment

0 Comments