የሴጋ ጉዳት



ሰላም የተወደዳቹ የሸገር 24ሚድያ ተከታታዮች እንደምን ከረማቹልን እያልን ዛሬ ይዘንላቹ የመጣነው ስለ ሴጋ ነው። ሴጋ (በወንዱም ሆነ በሴቷ) መፍትሄ እስካላገኘ ድረስ የእድሜ ልክ ክፉና ጎጂ ልማድ ነው። ይኽ ዐመል አንዴ ከተጠናወተ(ሴቷንም ሆነ ወንዱን) ለመተው እጅግ ከባድ ነው፤ ሴጋ አለመልቀቁ ሱሰኛም ማድረጉ አካላዊ፣ አእምሮኣዊና ስነልቦናዊ ጉዳትን ያመጣል፡፡
Men's Fashion Category

ሴጋና ልጆች
ሴጋ ከሚያስከትለው ዘለቄታዊ አንዳንዴም(በወቅቱ ካልቆመ) የእድሜ ልክ ችግር ከመሆኑ አንጻር ልጆች ወደ ጉርምስና እድሜያቸው እየተቃረቡ ሲሄዱ ስለወሲብ ጸጋነትና አግባባዊ አጠቃቀሙ መማር አለባቸው።
በተለይም አሁን ባለንበት ነባራዊ ዘመን የወንዶች ወንዳወንድነት ባሽቆለቆለበትና አባቶችም ወንዳወንድ ጠባይ በማያሳዩበት በዚህ ወቅት ልጆች በተለይም ሴቶች ልጆች ቶሎ ለመጎርመስና ለተሳሳተ የወሲብ ግንዛቤና ድርጊት ይጋለጣሉ።
ከዚህ በተጨማሪም ዘመን በወለዳቸው የቴክኖሎጂ ውጤት በሆኑ መሣሪያዎች የምናገኛቸው የወሲብ ትዕይንቶች ችግሩ ላይ ቤንዚን ያርከፈክፋሉ።
ምንም እንኳ ሴጋ በአብዛኛው የወንዶች ክፉ ልማድ ቢሆንም ከወሲባዊው አብዮት ወዲህ ግን የሚለማመዱት ሴቶቹም ቁጥር ጨምሯል።
አንተ ታዲያ ሚስትህንና ልጆችህን(ወንዱንም ሆነ ሴቷን) ስለወሲብና ትክክለኛ(አግባባዊ) አፈጻጸሙ፣ ስለሴጋም ጎጂነት ታስተምር ዘንድ አንተ መጀመሪያ አውቀኸው(ጉዳቱንም ጭምር) ራስህንም ጠብቀህ ልትገኝ ይገባል። በዚህም መሠረት ሚስትህም ሆነች ልጆችህ በዚህ ልማድ እንዳይገኙ ሥርዓትን ልትሠራላቸው፣ ልትመክራቸው ፈጽመውት ቢገኙ ደግሞ ልትቀጣቸው ይገባሃል።
የሴጋ ጎጂ ልማድነት(ከወንዶቹ አንጻር)
Health and beauty category 
     1ኛ.አካላዊ ጉዳት
ውዱ ወንድሜ! ሴጋ በቋሚነት የምትጠቀም ከሆነ የሰውነትህን ፈሳሽ፣ ወዝህን፣ ጉልበትህን አሟጦ ይጨርሰዋል። ይኽም ማለት ከሴጋህ በኋላ ሰውነትህ ይልፈሰፈሳል፣ አይንህ ይፈዛል(ስብር ይላል)።
ወሲብ ከሚስቴ ጋር ስፈጽም ይደክመኛል?” ብትለኝ አዎን ወሲብም ከሚስትህ ጋር ብትፈጽም ይደክምሃል። ነገር ግን ከእርሷ ጋር የምትፈጽመው ሰውነትህን የማይመጥ ጉልበትህንም የማይጨርስ ይልቁንስ መታደስ ያለበት ነው። ይኽ የሚሆነው ግን ከእርሷ ጋር የምትፈጽመው ወሲብ ሴጋን የሚያስረሳ እርካታውም የጋራ መሆን ያለበት ነው፡፡
የተለያዩ ጉዳቶች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ አንድ በአንድ እናያለን፦

    2ኛ. አእምሮአዊ ጉዳት

በተለይም በዚህ ዘመን ለሴጋ ወሲባዊ ትዕይንቶች ከፍተኛ መንሴዔዎች ናቸው። በስሜት ሕዋሶቻችን የተቀበልናቸውን መልእክቶች ተንተርሶ አስፈላጊው አጸፋዊ ምላሽ በሚመለከተው የሰውነት ክፍል እንዲሰጥ የሚያዘው አእምሮ ነው።
በወሲባዊ ትዕይንቶች የተነካው(መልእክት የተቀበለው) የአእመሮአችን ክፍል የልብ ምታችን እንዲጨምር፣ ደምም በፍጥነት እንዲዘዋወር (በተለይም ወደ ብልታችን) ከዚህም የተነሳ እንዲነቃቃ ያደርጋል።
ይኽን ልማድ ያደረገው አእምሮህ ታዲያ ሚስትህን ስታይ፣ ጠረኗ ሲሸትህ፣ ሰውነቷን ስትዳብስ(ስትዳብስህ)፣ ለወሲብም ወደምንጣፍህ ስትወጣ አእምሮህ ሰውነትህን ለማዘዝ ይዘገያል(አያዘውም)። ምክንያቱ ደግሞ እርሱ የሚያውቀውና የለመደው ስሜት መቀስቀሻ ሌሎች ወሲብ ሲፈጽሙ ማየት ነውና።


Health and beauty category 
     3ኛ.ስነልቦናዊ ጉዳት

ሴጋ “ወሲብ”ከተባለ አንተ በራስህ ለራስህ ብቻ የምትፈጽመው የምትወዳትን ሚስትህን ያላሳተፈ ነውና በራስወዳድነት ማዕበል እየተንገላታህ ለሚስትህ ያለህ ናፍቆትና ስስትም እየቀነሰ ይሄዳል።
አለባበሷን ማድነቅ፣ የናፍቆትና የፍቅር ቃላትን መናገር፣ ፈቃዷን መፈጸምና ፍላጎቷንም በአግባቡ ማርካት ይሳንሃል። ምክንያቱ ደግሞ የእነዚህ ምንጭ የሆነውን ወሲባዊ ስሜት (መነቃቃት) በሴጋ አድርቀኸዋልና ነው።

     4ኛ. ከሴት ያርቅሃል

ሴጋን በቋሚነት ለሚጠቀም ወንድ ሴቶችን መቅረብ(መጥበስ)፣ ማናገር(መጀንጀን) ይሳነዋል። የመጠየቅ፣ የመነጋገርና የመግባባት ብሎም የመፋቀርን ሽልማትና እርካታ በዋዛ በሴጋ ያገኘዋልና(ምንም እንኳ ሴጋ ለወሲብ ምትክ ባይሆንም)።

Health and beauty category 
   5ኛ. ወኔህን ይሰልበዋል

ፈርጀብዙ የሆነ አባወራዊ ሚናህን የምትወጣበትን ወኔ ይገድለዋል። እያደርም ለቤትህ፣ ለሚስትህ፣ ለልጆችህ ግድ የሌለህ በራስወዳድነት ባሕር ሰምጠህ እንድትቀርም ያደርግሃል።

   6ኛ. ለስንፈተ ወሲብ ይዳርግሃል

ትማሩበት ዘንድ ፈጣሪ የሰጠንን ጸጋ በአግባቡ ተጠቅመን በትዳርህ አንድነትን እንድናጠናክርበት ዘንድ ነው።
ሴጋ ለስንፈተ ወሲብ እንደሚዳርግህ ማወቅ ግድ ነው።

ምንጭ፦ዶ/ር ሰላሞን Baby products