ስንፈተ-ወሲብን የምንከላከልባቸው 15 መንገዶች
ሰላም ውድ የአምዳችን ተከታታዮች ዛሬ እንደሚከተለው ስለ ስንፈተ ወሲብ የምንከላከልበትን መንገዶች ይዘንላቹ መተናል።
እነዚንም በዝርዝር እናያለን፦
1) ክብደትን መቆጣጠር
ከፍተኛ የሰውነት ክብደት ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን እና የስኳር በሽታ ሊያስከትል ይችላል። እነዚህ ነገሮች የስንፈተ-ወሲብ መንስኤዎች ሊሆኑ ይችላሉ። አንድ ጥናት እንደሚናገረው የሆድ ስፋታቸው ከ100 ሴንቲሜትር በላይ የሆኑ ወንዶች በስንፈተ-ወሲብ የመጠቃት እድላቸው ከፍተኛ ነው። ክብደትን መቆጣጠር ስንፈተ-ወሲብን የምንከላከልበት አንዱ መንገድ ነው።

2) አመጋገብ
ስንፈተ-ወሲብ ብዙ ግዜ ከልብ በሽታ ጋር ተያያዥነት አለው። ለልብ የሚስማማ አመጋገብ ስንፈተ-ወሲብን ለመከላከል ይረዳል። የደም ቧንቧን በቆሻሻ የሚያጣብቡ ምግቦችን መቀነስ ያስፈልጋል። የወተት ምርቶችን፣ በዘይት ተነክረው የተጠበሱ ምግቦችን እና ቀይ ስጋን በመቀነስ ፍራፍሬዎች፣ አትክልት፣ አሳ እና የሆል ግሬይንስ ምግቦችን መመገብ ይመከራል።
3) ደም ግፊትን መቆጣጠር
ከፍተኛ ደም ግፊት የደም ቧንቧዎችን በማጥበብ የደም ዝውውር ላይ ጫና ይፈጥራል። ወደ ብልት የሚሄደው ደም ሲቀነስ ለግንኙነት መነሳት ይከብደዋል። የደም ግፊት መጠንዎን ለክተው የማያውቁ ከሆነ እንዲጀምሩ ይመከራል። ከፍተኛ ደም ግፊት እያለዎ ሳያውቁት እየኖሩ ይሆናል።
4) የኮሌስትሮል መጠን መቀነስ
ደም ቧንቧ በኮሌስትሮል ጥርቅም ምክንያት ሲጠብ ደም ዝውውር በአግባቡ አይከናወንም። ይህ ሲሆን ብልትን ለግንኙነት ማስነሳት ይቸግራል። የኮሌስትሮል ልኬትዎ ከፍተኛ ከሆነ ስለመቀነሻ መንገዶች ዶክተርን ማማከር ተገቢ ነው። ከአመጋገብ ለውጥ በተጨማሪ መድሃኒት ሊታዘዝ ይችላል።
5) ስኳርን በቁጥጥር ስር ማዋል
የስኳር በሽታን በአግባቡ አለመቆጣጠር ስንፈተ-ወሲብን ሊያስከትል ይችላል። ከፍተኛ የደም ስኳር ብልት ውስጥ የሚገኙትን ደም ቧንቧዎች እና ነርቮች ላይ ጉዳት ሊፈጥር ይችላል። ዶክተር በማማከር የስኳር መጠንዎን በቁጥጥር ስር ማዋል ይችላሉ።
6) ማጨስ ማቆም
የሚያጨሱ ወንዶች በስንፈተ-ወሲብ ችግር የመጠቃት እድላቸው እጥፍ የጨመረ ነው። ማጨስ የደም ቧንቧዎችን በማጥበብ የግንኙነት ህይወታችንን ሊያውክ ይችላል። የስንፈተ-ወሲብ መድሃኒቶች በሚያጨሱ ሰዎች ላይ ውጤታማነታቸው ዝቅተኛ ነው።
7) ከመጠን በላይ አለመጠጣት
መጠጥ እና ግንኙነት ሁሌም አብረው አይሄዱም። አብዝቶ መጠጣት የግንኙነት ችሎታዎን ያዳክማል። መጠጥ የአልጋ ስር ችግር ሲሆን መጠኑን መቀነስ ይመከራል።
8) ከአደንዛዥ እጽ መቆጠብ
ብዙ አደንዛዥ እጾች የስንፈተ-ወሲብ መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ። እጾች ነርቨስ ሲስተምን በማደብዘዝ፣ ሲበረታ ደግሞ የደም ቧንቧዎችን በመጉዳት ስንፈተ-ወሲብ ሊያስከትሉ ይችላሉ።
9) አካል ብቃት እንቅስቃሴ
አካል ብቃት እንቅስቃሴ ለግንኙነት ብዙ ጠቀሜታዎች አሉት። ልብ እና ደም ቧንቧዎች ጤነኛ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ ክብደት እንዳይጨምር ይከላከላል፣ ጭንቀትን ያስወግዳል፣ በአጠቃላይ ጥሩ ጤና እንዲኖረን ያደርጋል። እንቅስቃሴው ከፍተኛ ሃይል የሚጠይቅ መሆን የለበትም። በየቀኑ የሚደረግ የ30 ደቂቃ ዎክ የስንፈተ-ወሲብ ተጋላጭነትዎን እንደሚቀንስ ጥናቶች ይናገራሉ።
10) የቴስቶስትሮን መጠንዎን መከታተል
ከ30 አመት እድሜ በኋላ የሰውነት ቴስቶስትሮን መጠን መውረድ ይጀምራል። እድሜ በገፋ ቁጥር መውረዱን ይቀጥላል። በጣም ዝቅተኛ ደረጃ ሲደርስ የግንኙነት ፍላጎትዎን ያደበዝዛል። ስንፈተ-ወሲብም ሊያስከትል ይችላል። የቴስቶስትሮን መጠንዎን በቀላል የደም ምርመራ ማወቅ ይችላሉ።

11) አናቦሊክ ስቴሮይድ መጠቀም
ቴስቶስትሮን መወጋት የግንኙነት ችሎታዎን ቢጠቅም ነው እንጂ አይጎዳም ብለው ሊያስቡ ይችላሉ። ቴስቶስትሮን መወጋት የሰውነትዎን ቴስቶስትሮን ማመንጨት አቅም ይቀንሳል። በዚህ ምክንያት ቴስቶስትሮን መወጋት ሲያቆሙ ስንፈተ-ወሲብ ሊከተል ይችላል። ሌሎች የጤና ችግሮች ሊከተሉም ይችላሉ። የዘር ፍሬ መቀነስ፣ መመለጥ ሊከሰቱ ይችላሉ።

12) ጭንቀትን መቆጣጠር
በስራ፣ ወይም ከሰው ጋር ባለዎ ግንኙነት ወይም በህይወት ላይ በተፈጠረ ለውጥ ምክንያት ጭንቀት ውስጥ ከገቡ የግንኙነት ህይወትዎ ሊጎዳ ይችላል። ስንፈተ-ወሲብ ካጋጠመዎ እራሱ ሌላ ጭንቀት ይሆንብዎታል። ጤነኛ የግንኙነት ህይወት እንዲኖረን የጭንቀት መጠናችንን መቀነስ ይኖርብናል።
13) የእንቅልፍ በሽታ
ስሊብ አፕኒያ ተብሎ በሚታወቅ የእንቅልፍ ህመም ሳቢያ ለስንፈተ-ወሲብ ልንጋለጥ እንችላለን። ለዚህ ህመም ህክምና ስናደርግ የስንፈተ-ወሲብ ችግራችን አብሮ እየቀነስ ሊመጣ ይችላል። የእንቅልፍ ህመም አለብኝ ብለው ካሰቡ ዶክተር ከማማከር ወደ ኋላ አይበሉ።
14) የመድሃኒት ተጽእኖ
የሚከተሉት መድሃኒቶች ስንፈተ-ወሲብ ሊያስከትሉ ይችላሉ።
• ዳዩሬቲክስ
• ጸረ-ድብርት መድሃኒቶች
• ጡንቻ የሚያላሉ መድሃኒቶች
• የካንሰር መድሃኒቶች
• አንቲሂስታሚንስ
• ኦፒዮይድ ህመም አስታጋሾች
15 ቀዝቃዛ ሻወር መውሰድ
ብዙዎቻችን የሻወር ጥቅም ከሰውነትን ከማፅዳት የዘለለ አይመስለንም ነገር ግን ቀዝቃዛ ሻወር በምንወስድበት ጊዜ ሰውነታችን ውስጥ ያለው የደመ የዝውውር ስርአት ይፋጠናል ጤናማ የሆነ ሪያክሽን ይካሄዳል ለወሲብም የመነሳሳት ጉዳይም ይጨምራል።

0 Comments