ሴቶች የሚረኩበት የወንድ ልጅ የብልት መጠን


ጥንዶች መሃከል የግንኙት ሂደት ላይ ተጽዕኖ ያመጣል ብሎ ከሚታሰበው ችግር ውስጥ አይምሯችን ውስጥ የሚመጣ ነው የብልት መጠን ማነስ፤ ይህ ተጽዕኖ ግን ብልት በማነሱ ሳይሆን በስነልቦና ጫናውና ይህን ጫና ለመቀነስ በሚተገብሯቸው ችግሮች ምክንያት የሚፈጠር ነው ፡፡
Deal of the day
አብዛኛውን ጊዜ በተፈጥሮ ወንዶች ባላቸው የብልት መጠን አይረኩም። ማንኛውም ወንድ ምንም እንኳ ብልቱ ረዘም ያለ ወይም ትልቅ የሚባል አይነት ቢሆን እንኳ “ ምነው ትንሽ ረዘም ባለልኝ” ብሎ መመኘቱ አይቀሬ ነው። ይህም የሚሆነው ከሌሎች ጋር በሚያነጻጽሩበት ወቅት ነው ፡፡ ለምሳሌ ፦ሁለት ወንዶች ራቁታቸውን በዋና ቦታ፣በመፀዳጃ ቤት ወይንም በፍል ውሃ አካባቢ ሲገናኙ ብልቶቻቸውን ፈጥኖ የመመልከትና ከራስ ጋር የማመዛዘን ችግር ይስተዋላል። በዚህ ሁኔታ የእሱ ትልቅ እንደሆነ የተረዳው እንኳ ሌላ ቦታ ከሱ የሚበልጥ ሲያገኝ ብልቴ ትንሽ ነው የሚል ፍርሃት ያድርበታል። ብዙ ጊዜ መጠንን የተመለከቱ ጥያቄዎች ይነሳሉ።


በዋናነት ማወቅ ያለብን ነገር የብልት ማነስና መተለቅ ብልት ከሚጠበቅበት ስራ ጋር ግንኙነት እንደሌለው ነው። እውነታው ግን የወንድ ብልት ርዝማኔ በሴቷ ብልት ውስጥ መግባት ከቻለ በቂ ነው።በሌላ አነጋገር የዘር ፍሬውን በትክክል ወደ ብልቷ ማድረስ ከቻለ የሚፈለግበትን አሟልቷል ማለት ነው።
Home Category
ምክንያቱም የአንዲት ሴት እርካታ የሚፈጠረው በብልቷ ቀራብ ክፍሎች ማለትም ወደ ውስጥ ሳይጠልቅ በመካፈቻው ላይ ባሉት የብልቷ ክፍሎች ስለሆነ የወንዱ ብልት መተለቅና መወፈሩ ሴቷ በወሲባዊ ግንኙነት ጊዜ በምታገኘው እርካታ መካከል ምንም ግንኙነት የለውም።ስለዚህ ማንም አቅመ አዳም የደረሰ ወንድ ሌላ ችግር ከሌለበት በስተቀር ባለው የብልት መጠን ሴትን ማርካት ይችላል።

የብልት ርዝመትና ውፍረት ከሰው ሰው ይለያያል። እንዲሁም ለግንኙነት ያለው ዝግጁነት፣ ሙቀት፣ የግንኙነት ድግግሞሽ ከሰው ሰው በልኬት ወቅት የመጠን ልዩነት ከሚያመጡት ምክንያቶች ይጠቀሳል፡፡

የብልት መጠን በተሰራ ጥናት መሰረት አማካይ የአንድ ወንድ ለግንኙነት ዝግጁ ያልሆነ የብልት መጠን እርዝማኔ 9-10ሴ.ሜ (3.5-3.9 ኢንች) ነው፡፡
Kids Category
ለወሲብ የተዘጋጀ ወይም የተንሳ የብልት አማካኝ ርዝማኔ 12.9-13.6ሴ. ሜ (5.1-5.4ኢንች) ሲሆን ዙሪያው ደግሞ 11.66 ሴ.ሜ (4.59 ኢንች) ባለው ውስጥ ይገኛል። ነገር ግን ከዛም በላይ ወይም በታች የብልት መጠን ያላቸው ወንዶች ይኖራሉ። በዚህ ወቅት መጠነ ዙሪያውን ሲለኩ የብልት የመሃከለኛውን ክፍል ልኬት መውሰድ ይኖርቦታል ፡፡

ወንዶች ላይ የብልት መጠን ልዩነት መኖሩን ከተረዳንና ሴት ልጅን ለማርካት የብልት መጠን ወሳኝ ነገር እንዳልሆነ ካወቅን ብልቴ አነስተኛ ነው የምንል ሰዎች ከአጉል ፍርሃት መላቀቅ ይኖርብናል።

አብዛኛውን ጊዜ ሴትን የሚሸሹ ወንዶች ዋናው ምክንያታቸው ብልቴ አነስተኛ ነው ብለው ማመናቸው ነው። ለዛም ነው ስሜታቸውን በተለያየ መንገድ ለማብረድ የሚሞክሩት ያ መሆኑ ደግሞ ለተጨማሪ የስነ ልቦና ችግርና ለስንፈተ ወሲብ ተጋላጭ ያደርጋል።

Everything on JUMIA ለምሳሌ አብዛኛውን የግለ-ውሲብ ተጠቃሚ የዚህ ችግር ተጋላጭ ነው። የብልት ማነስ የወሲብ ህይወት እንቅፋት እንዳልሆነ እና መሰረታዊውን እርካታ ስለማይከለክለን እንዳንጨነቅ እንዲሁም የብልት መተለቅ የብቃት ማረጋገጫ እንዳልሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል ፡፡