ከሰሞኑ ከህዝብ ዕይታ ርቀው የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን ጎበኙ፡፡



በተለያዩ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች አካላቸው ለጎደለ ኢትዮጵያዊያን የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ በማምረት የሚያቀርበው ድርጅቱ በጤና ሚኒስቴር ሥር በቅዱስ ጳውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚገኝ ነው እንደ ኢቢሲ ዘገባ፡፡የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህዝብ ዕይታ መራቅ ከሰሞኑ ሲያነጋግር ነበረ፡፡ Computing Category ጤና እክል ገጥሟቸው ሊሆን እንደሚችል በመገመትም ብዙዎች ጭንቀታቸውን ሲገልጹ ተስተውለዋል፡፡በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ሲራገቡ የነበሩ ያልተረጋገጡ መረጃዎች ለዚህ መንስዔ ናቸው፡፡የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ይሄንኑ ጉዳይ በማስተባበል ዶ/ር ዐቢይ በተሟላ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ማስታወቁም የሚታወስ ነው፡፡


ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ለተጎዱ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና ለሲቪሎች የሚሠራውን ሰው ሠራሽ አካል ዛሬ ጎብኝተዋል‼️


ጠ/ሚንስትሩ "በሕግ ማስከበር ሂደቱና በሌሎችም ጊዜያት የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው በበጎ ፈቃደኞችና በድርጅቱ ባለሞያዎች የሚከናወነውን የሰው ሠራሽ አካል ማምረቻ ድርጅት ሠራተኞች የሚደነቅ ሥራ እየሠሩ ነው። ከውጭ መጥተው በበጎ ፈቃደኝነት ይሄንን ታላቅ ሥራ የሚሠሩ ሰሎሞን አማረን የመሰሉ ወገኖች ሊበረታቱ ይገባል" ብለዋል።