Hyperloop ቴክኖሎጂ ምንድነው?
ሃይፐርሎፕ ለሁሉም ክፍት የሆነ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ነው:- ኤለን መስክ እና ስፔስ ኤክስ የመሠረቱት ሲሆን ሌሎችም ኩባንያዎች ይህንን ቴክኖሎጂ አንዲያዳብሩት ያበረታታሉ።

ይህ ቴክኖሎጂ 1000km/h ፍጥነት ያለው ሲሆን ሞተር እና የአየር መግፊያ(air compressors) ጥምር ይጓዛል፡፡ በሌላ አገላለጽ በአየር ላይ አንደመሄድ ማለት ነው!
በርካታ የሃይፐርሎፕ አይነት ሞደሎች አሉ:- እስካሁን ድረስ ሶስት ኩባንያዎች የሃይፐርሎፕ የመጓጓዣ ዘዴን ለመፍጠር በስራ ተጠምደዋል።
የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ሃይፐርሎፕን ከመሄድ አይገታውም:- ምክንያቱም የሊቲየም-አዮን ባትሪ ስለተገጠመለት።በርካታ ሀገሮች ሃይፐርሎፕን ለመተግበር የመጀመሪያው ለመሆን እየተዋጉ ነው:- እነዚህም አውስትራሊያ ፣ ህንድ ፣ ሩሲያ ፣ ስሎቫኪያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ይገኙበታል ፡፡ የመጀመሪያው ማን ነው? ለማለት ይከብዳል ፣ ግን ሩሲያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሁለቱም ጥሩ እድል ያላቸው ይመስላሉ ፡፡

ሃይፐርሎፕ እ.ኤ.አ. እስከ 2022 በአለም ውስጥ በየትኛውም ስፍራ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይታመናል።ሃይፐርሎፕ ለየትኛውም የአየር ሁኔታ ተስማሚ መጓጓዣ ነው:- ምክንያቱም በቱቦ ውስጥ ስለሆነ ለ ነፋስ፣በረዶ፣ጭጋግ፣ሙቀት እና ዝናብ የተጋለጠ አይደለም።ይህ የማጓጓዝ ፅንሰ-ሀሳብ አዲስ አይደለም:- እንግሊዛዊው የፈጠራ ሰው George Medhurst በ 1799 የቱቦ መጓጓዣ ስርዓት የፈጠራ ባለቤትነት ማረጋገጫ መሰጠቱ ያስገርም😲 ይሆናል!
0 Comments