Photo credit:tekiva ethiopia

በአዲስ አበባ ቦሌ ዘ ሃብ ሆቴል አካባቢ የእሳት አደጋ ተከሰተ።

አደጋው ከደቂቃዎች በፊት ታምሪን መኪና መሸጫ አካባቢ ዘ ሀብ ሆቴል ፊት ለፊት ባለ አንድ መኖሪያ ቤት መድረሱን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ገልጿል።

Fashion አደጋውን በቁጥጥር ሰር ለማዋል የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም የአካባቢው ሰዎች የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ሲሆኑ የእሳት እና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች በቦታው ደርሰው አደጋውን በቁጥጥር ስር ለማዋል በጥረት ላይ ናቸው።

በሌላ በኩል ፦

በአዲስ አበባ ኡራኤል አካባቢ በመኖርያ ቤቶች ላይ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ደርሷል።

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በቦሌ ክፍለ ከተማ ኡራኤል አካባቢ በሚገኙ መኖርያ ቤቶች ላይ ድንገተኛ የእሳት አደጋ መድረሱን አስታውቋል።

Health and beauty category ባሁኑ ሰአት የእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8