እርግዝና እና ወሲብ 


የብዙ ባለትዳሮች ተግዳሮት ወሲብ እና እርግዝና በእርግዝና ወቅት ስለሚገጥም የወሲብ ፍላጎት በስሱ እናያለን በጥሞና ያንብቡ።
በእርግዝና ወቅት ስለ ወሲብ ማሰብ ለነብሰጡር ሴቶች የመጨረሻው ከባድ ተግባር ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይ በማቅለሽለሽ እና በማስመለስ እንዲሁም ድካም በሚበረታበት በዚህ ወቅት አንዳንድ ሴቶች የወሲባዊ ግንኙነት ፍላጎታቸው ሊቀስቅስ ይችላል፡፡ የወንድ ተጣማሪያቸውም በተመሳሳይ አንዳንዶች ግንኙነቱ ስሜትን በማስቀደም ብቻ ሊፈፅሙት ሲነሳሱ ሌሎቹ ወንዶች በአንፃሩ ህፃኑን እና ነብሰጡር ወዳጆቻቸውን ላለመጉዳት በማሰብ ወሲባዊ ግንኙነትን በዚህ ወቅት በእጅጉ የሚፈሩት ተግባር ይሆናል፡፡ አልጋ ለይቶ የማደር ሃሳቡ የሚመነጨውም ለዚሁ ሊሆን ይችላል፡፡ Deal of the day በአሜሪካ ኖርዝ ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ አሶሽየት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ዳይና ሳለሰች ‹‹በእርግዝና ወቅት ወሲባዊ ግንኙነት ማድረግ ጥሩም መጥፎም ዜና ይዞ የሚመጣ ሊሆን ይችላል›› ይላሉ፡፡ የሴቶቹ እርግዝና ያልተወሳሰበ መሆን እና ዝቅተኛ አደጋ የሚያስከትል መሆኑ ሲረጋገጥ እንዲሁም የተጓዳኞች የግል አተያይ መሰረታዊ መሆኑን ከግምት እንድናስገባ ይመክሩናል፡፡ አንዳንዶች በዚህ ወቅት ወሲብን ይበልጥ ሲያጣጥሙት ሌሎች ደግሞ ዝቅተኛው የደስታ ምንጭ አድርገው ይወስዱታል፡፡ በመጀመሪያዎቹ የእርግዝና ወቅቶች ማለትም ሴቶች የማጥወልወል እና የድካሙ ስሜት ውስጥ ሲሆኑ ብዙዎቹ ከፍተኛ ወሲብ ፍላጎት አያሳዩም ነው ባለሙያዋ የሚሉት፡፡ በሁለተኛው ዙር የእርግዝና ወቅት ደግሞ በአንፃራዊነት የተሻለ የሚባል ስሜት ውስጥ ይገባሉ፡፡ በተለይ የመራቢያ አካላቸው ላይ በተለየ ሁኔታ የሚመነጨው ዘይትም ለወሲባዊ ግንኙነት ይበልጥ እንዲሳቡ ምክንያት ይሆናል ባይ ናቸው፡፡ በዚህ ወቅት ነብሰጡር ሴቶች ከወሲባዊ ግንኙነት ብዙ እንዲርቁ ከሚያደርጋቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ ደግሞ ሆዳቸው በዚህ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ የክብ ቅርፅ የሚይዝ በመሆኑ ነው፡፡ Health and beauty category ይሄ በሶስተኛው የእርግዝና ዘርፍ የሚጠበቅ አይደለም፡፡ ሆድ ሲገፋ እንዲሁም ድካምም በእጅጉ ሲበረታ የወሲብ ስሜቱ በዛው ልክ እየቀዘቀዘ ይመጣል፡፡ ዶ/ር ሳላሰች እንደሚሉት ባለቤት የፍቅር ጓደኛ ወደ መጨረሻዎቹ ወራት እየተቃረበች ከመጣችው ከነብሰጡር ጓደኛ ጋር ወንዱ ወሲባዊ ግንኙነት የማድረግ ፍላጎቱ ከተነሳሳ ብዙ መጨነቅ አይገባም ይላሉ፡፡ በእንቁላሉ በሚገባ የተከለለ በመሆኑ ህፃኑ በምንም መልኩ ለአደጋ የተጋለጠ ሊሆን አይችልም እና፡፡ ባለሙያዎች ሴቶች በእርግዝና ምክንያት ለውጥ ውስጥ ሲያልፉ ለትዳር አጋራቸው አሁንም ያልበረደ ፍቅር እንዳላቸው ማሳየት፣ እርስ በርስ የመግባባት መስመሩም በተሻለ መንገድ እንዲቀጥል ማድረግ ይኖርባቸዋል ይላሉ፡፡ በዕርግዝና ወቅት ወሲባዊ ግንኙነቱ በምን መልኩ ሊቀጥል ይገባል? ሴቷ የእርግዝና ወቅቷ እየጨመረ እና ሆዷም እየገፋ ሲመጣ ባህላዊና የተለመደው ወሲባዊ ቅርፅ ማለትም ወንዱ ከላይ የመሆን አቅጣጫ ምቾት የሚሰጣት አይሆንም፡፡ በዚህ ምክንያት ሳልስቼን ጨምሮ የዘርፉ ባለሙያዎች ከመሀል ወይም ፊት ለፊት የመተኛት የግንኙነት አቅጣጫዎችን ብቻ መጠቀም እንደሚገባ ያስገነዝባሉ፡፡ ከዚያ ባለፈ ባሎቻቸው በጀርባቸው እንደተኙ አጠቃላይ የወሲባዊ ግንኙነትን ሂደት ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር በሚችሉበት አቅጣጫ ማለትም ከላይ እንዲሆኑ ይመከራል፡፡ በተወሰኑ ደረጃዎችም ነብሰጡር ሴቶች በጀርባቸው ብዙ እንዳይተኙ ይመከራሉ፡፡ ምክንያቱም የለብ ምት እና የደም ግፊትን ሊያስከትሉባት የሚችሉት ሰፓይን የሀይፐርቴንሲቭ ሲለንድሮምን ያስከትላልና፡፡ ችግሩ በተለይ ሴቷ በሶስተኛው እርግዝና እርከን ላይ ስትገኝ ይበልጥ የከፋ የመሆን ዕድል አለው፡፡ በግንኙነት ወቅት ምንም አይነት ችግር የማይገጥማት እናት ያለ ችግር በሂደቱ መቀጠል ትችላለች፡፡ ነገር ግን ከወሲብ በኋላ መድማትና ሌሎች ህመሞች የሚከተሉ ከሆነ የቀይ መስመሩ እየታለፈ ስለመሆኑ ማሳያ ነው እና በአፋጣኝ የህክምና ዶክተሮችን ማማከሩ ተገቢ ነው፡፡ ነብሰጡር ሴቶች በመሰል ግንኙነት ወቅት በትልቁ ትኩረት ይሰጡበት ዘንድ ባለሙዎች ከሚያስጠነቅቁት ሁኔታ መካከል አንዱ በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት በሚተላለፉ በሽታዎች የተጠቃ የትዳር አጋር ካላቸው ኮንዶምን ጨምሮ ሌሎች መከላከያ መንገዶችን በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት እንዲጠቀሙ ነው፡፡ ባለሙያዋ በፆታዊ ግንኙነት ወቅት ነብሰጡር ሴቶች በተቻለ መጠን ሰውነታቸውን ማዳመጥ እና ከጓደኛ ጋር ግልፅ የመሆንን አስፈላጊነት ያሰምሩበታል፡፡ በሌላ መልኩ ነብሰጡር እናቶች በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ሊያገረሹ የሚችሉ ኢንፌክሽኖች ተጋላጭ የመሆን ስጋት ካለባቸውና የተቃራኒ ፆታ አጋራቸው ትብብርም የሚፈልጉትን ያህል ካልሆነ በራሳቸው የሌቴክስ የሴቶች ኮንዶምን በግንኙነት ወቅት መጠቀም እንደሚኖርባቸው ዶ/ር ያስገነዝባሉ፡፡ ኮንዶሞች ውጤታማ ካልሆኑ ደግሞ ሌሎች የሴት ኮንዶሞችን መሞከር ጠቃሚ ነው፡፡ ደጋግመው ሁሉም ባለሙያዎች የሚያሳስቡት በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ምቾት የሚነሱ ሁኔታዎች ነብሰጡር ሴቶች ሲገጥማቸው በተቻለ መጠን ለተጣማሪያቸው ወዲያው ማሳወቅ ያለባቸው መሆኑን ነው፡፡ የወሲብ ስሜቱ ቢኖር እና በሌላ መልኩ በተለመደው መልኩ ግንኙነቱን ማድረግ አስቸጋሪ ከሆነ ደግሞ ሌሎች የስሜት መቆጣጠሪያና ኤሮቲክ ተግባራትን ማጤን ይመከራል፡፡ ከወሲብ እኩል ስሜታችንን ልናቀዘቅዝባቸው የምንችላቸው እንደ መሳሳም፣ መተቃቀፍ፣ እና መተሳሰቡ በራሱ የተሻሉ መፍትሄዎች ናቸው፡፡ ወሲባዊ ግንኙነት በእርግዝና ወራትም የሚቀጥል ተፈጥሯዊ ጉዳይ ነው፡፡ Health and beauty category ባለሙያዎቹም ደጋግመው ጤናማ እርግዝና የሚያሳልፉ ሴቶች መሰል ግንኙነት በራሳቸውም ሆነ በተሸከሙት ልጅ ላይ ሊከሰት የሚችል ችግር አይኖርም፡፡ በተፈጥሮ መጠበቂያ ግንቦች በሚገባ የተከለለ በመሆኑ፡፡ አንዳንዶቹ የህክምና ባለሙያዎች ነብሰጡሮች ወሲባዊ ግንኙነትን በመጨረሻዎቹ የእርግዝና ወራት እንዲያስወግዱ ይመክራሉ፡፡ ሊከሰት የሚችለውን ችግር በሚገባ በማስረዳት ረገድ ርቀው መሄድ ባይችሉም፡፡ በእርግዝና ወቅት ወሲባዊ ግንኙነትን እንድናስወግድ የሚያስገድዱ ምክንያቶች ሐኪሞች ከዚህ በታች የተዘረዘሩና በእርግዝና ላይ አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ችግሮች ካሉብሽ ወሲብን እንዳትፈፅሚ ሊከለክልሽ ይችላል፡፡ – የመራቢያ አካል ላይ የሚከሰት የመድማት ችግር ካለብሽ – መንታ አልያም ከሁለት በላይ ልጆችን እንደምትወልጂ ተነግሮሽ በዛ መሰረት የመውለጃ ጊዜሽን እየጠበቅሽ ከሆነ (ከ37 ሳምንታት በፊት) የመውለድ ስጋት እና ታሪክ ካለሽ – የማህፀንሽ በር ያለ ጊዜ የመለጠጥ እና የመከፈት ምልክት የሚያሳይ ከሆነ… ልጅሽን ከወለድሽ በኋላ መቼ ነው ወደ ግንኙነት መመለስ ያለብሽ? ልጅሽን በተፈጥሮ መንገድ፣ በቀዶ ጥገናና ወይም በሌላ የህክምና እርዳታ ከወለድሽ በኋላ ሰውነትሽ ስለሚዳከም ለማገገምና ወደ መደበኛው የወሲብ ህይወት ለመመለስ ጊዜ መውሰድ ይኖርብሻል፡፡ Women's Fashion Category ብዙዎቹ የጤና ባለሙያዎች ከወሊድ በኋላ ሴቶች በትንሹ እስከ 6 ሳምንት ከመሰል ግንኙነት መታቀብ አለባቸው በሚለው የጊዜ መመሪያ ላይ ይስማማሉ፡፡ የጊዜ ገደቡ ሴቷ የማህፀን በሯ ወደ ቀድሞ ቦታው እንዲመለስ ቁስሎችም እንዲሽሩ ይረዳል፡፡ ወደ መደበኛ ወሲባዊ ህይወትሽ ስትመለሺ ግንኙነቱን ቀስ ብለሽ መጀመር ይኖርብሻል፡፡ ያልተፈለገ እርግዝናን እና ኢንፌክሽኖችን እንዲሁም የአባላዘር በሽታዎች የመጠቃት እድሉ አሁንም ያለብሽ እንደሆነም መድሐኒቶችን እና መከላከያዎችን መጠቀም ይኖርብሻል፡፡