#Axum #Shire
የአክሱምና ሽሬ ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዛሬ ማምሻውን አግኝተዋል
በትግራይ ክልል በህወኣት ቡድን ጉዳት ደርሶበት የነበረው የኤሌክትሪክ መስመር ተጠግኖ የአድዋ፣ አክሱምና ሽሬ ከተሞችና አካባቢያቸው ዛሬ የኤሌክትሪክ አገልገሎት ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቃል።
መሠረተ ልማቱን ለመጠገን በተደረገው ከፍተኛ ጥረት ቀደም ሲል አብዛኞቹ የትግራይ ኣካባቢዎች የመብራት አገልግሎት ማግኘታቸውንና የአድዋ ከተማ ደግሞ ዛሬ ከሰዓት በፊት ኤሌክትሪክ ማግኘቱ ይታወሳል።
በህወኣት ቡድን ጉዳት ደርሶበት ከጥቅም ውጭ ሆኖ የቆየው የአክሱምና ሽሬ ከተሞችና አካባቢያቸው የኤሌክትሪክ መስመር በመጠገኑ ማምሻውን ከተሞቹ የመብራት አገልገሎት አግኝተዋል።
የሑመራ እና ወልቃይት ከተሞችና አካባቢያቸውን ኤሌክትሪክ ለማገናኘትም ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።
በዚህ አጋጣሚ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በመሆን የጥገና ስራውን በኋላፊነት ስሜት የተወጡ የተቋሙ ሠራተኞችን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ በተቋሙ ሥራ አመራርና ሰራተኞች ስም ማመስገዳቸውን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።

0 Comments