ኢትዮጽያ - የተዘነጋችው ገነት


 ኢትዮጽያ - የተዘነጋችው ገነት


#Ethiopia | ረ.ፕሮፌሰር አደም ካሚል

#Nebiyu Sirak  

ለሀገሬ ባለኝ አቅም ማበርከት አለብኝ የሚል ምኞት ከፈጠሩብኝ ጉምቱ ምሁራን መካከል ጋሽ አደም ልዩ አርአያዬ ናቸው። "አረብ አገራት ከኢትዮጵያ ያላወራረዱት ግዙፍ ዕዳ አለባቸው። በትኩረት ብንሰራበት ኖሮ የግብፅ ሴራ እንዲህ ለዘመናት አይተበትበንም ነበር" የሚል ንግግራቸው የሞተር ያህል ያነቃቃኝ ነው። 


"ግብጽ ዲፕሎማቶቿን እያላከች ኢትዮጵያ ግድብ ሰርታ በረሃብ ልትቀጣኝ ነው እያለች ስማችንን እያስጠፋች ትገኛለች፡፡ የግብጽን ቅስቀሳ የሰሙ አንዳንድ አረብ አገራት 'እውነቷን ነው ከግብጽ ጎን ነን' በማለት በበደል ላይ በደል እየጫኑብን ነው"  ይላሉ ጋሽ አደም፤


ይቀጥላሉ፦ ‹‹በሳዑዲ ዓረቢያ የንጉሥ አብዱልአዚዝ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበርኩበት ወቅት መምሕሬ የነበሩ ሰው የሐበሻ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ መሆኔን እንዳወቁ እንዲህ አሉኝ፤ 'እናንተ ሐበሾች በእስልምና እና በአረቡ ዓለም ያላችሁን ክብርና ደረጃ ራሳችሁ አውቃችሁ ለሌላው አለማሳወቃችሁ ሳያንስ፣ ስለ እናንተ የተፃፈላችሁን እንኳ አንብባችሁ መረዳት አልቻላችሁም' በማለት የተናገሩኝ ቃል ውስጤን ሲቆጠቁጠው ኖርኩኝ፤" ሲሉም ያወሳሉ


"ከዩኒቨርሲቲው ተመርቄ በባሕረ ሰላጤው ሀገሮች በኮንትራክተርነት ሙያ  በምሠራባቸው ጊዜያት አንድ ግብፃዊ ኢንጂነር ባልደረባየ በጨዋታ መሀል እንዲህ አለኝ፡፡ 'ቢላል አል ሐበሺ ግብፃዊ ቢሆን ኖሮ፣  በየዓመቱ በሀገራችን በያመቱ በስሙ ብሔራዊ በዓል ቀን በሰየምን ነበር' አለኝ።" Baby products የሚሉት ተመራማሪው ይህ ቁጭት ተፈላጊ መረጃዎች የሚገኙት በዓረብኛ ቋንቋ ስለሆነ በተለያዩ የዓረብ ሀገሮች በሚገኙ የታወቁ የመዳሕፍት መደብሮችና ቤተ መጻሕፍት እየተዘዋወሩ 25 አመታት የተሻገረ የማሰባሰብ እንቅስቃሴዬ ጀመሩ። ከሩብ ምዕተ ዓመት የማሰባሰብ ዘመቻ በኋላ ባዘጋጁት የመጀመሪያ ጥናታዊ መጽሐፋቸው በቁጥር 1 ውስጥ ብቻ ተከታዮቹ ጉዳዮች ተካተውበታል፦


* የኢትዮ ዓረብ ጥንታዊ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት

* ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ስልጣኔ በአካባቢው ምስራቅና ሰሜን ሀገሮች ያለው አሻራ

* የእስልምና ስደት ወደ ሐበሻ ዓላማው፣ ዕቅዱና ውጤቱ፣

* ሐበሾች በቁርአን፣ በሀዲስና በነብዩ (ሰዐወ) የተሰጣቸው ክብር፤ ወዘተ...

     ጋሽ አደም  የግብጾችን የጅራፍ ጩኸት በእኩል አቅምና በሚሰሙት ቋንቋ፣ መመከት የሚያስችሉን የዲፕሎማት አቅምን የገነቡ ናቸውና ልንጠቀምባቸው ይገባናል።


"የሀገር ሀብት ሆኖ የዘለቀ ነገር ግን ያልተጠቀምንበት፤ በአረብ ሀገርና መካከለኛው ምስራቅ ዲፕሎማሲያችን ለማጎልበት አገራችን ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት አይነት  ልሂቅ ናቸው" ያለው ጋዜጠኛው፣  "የዲፕሎማሲ ግንኙነታችንን  የሚያሳካው አምባሳደር የዜጎችን መብት ከማስከበር ጀምሮ  የተበላሸ ገጽታችን ማስተካከል መቻል ይጠበቅበታል፤ ለዚህ ስኬትም  ጋሽ አደም ሁነኛ ልሂቅ ናቸው፤ በዲፕሎማሲው መስክ መንግስት  ከዚህ በፊት የተጓዘበት የእከከኝ ልከክልህ ሹመት መቅረት አለበት፤ መመዘኛው የፖለተካ አቋም ሳይሆን ክህሎትና እውቀት እንዲሁም ልምድ መሆን አለበት" በማለት ጋዜጠኛ ነብዩ ምክረ ሐሳቡን ጠቁሟል።


"የተረሳችው  ገነት" በማለት ኢትዮጵያን የሚገልጿት ረ.ፕሮፌሰር አደም "ከትውልድ ትውልድ ፈተና ያልተለያት፣ ልዩና የማይጠገብ የተፈጥሮ ሀብት የታደለች፣ ሰፊ የወጣት ጉልበት የሚገኝባት..." ይላሉ የሚለው የበጎ ተግባር አጋፋሪና  ጋዜጠኛው  ነብዩ ሲራክ ነው። Baby products እሳቸውን የሚያውቃቸው የአፍሪካ ቀንድ መጽሔት ወጣት ሪፖርተር በነበረበት ወቅት ጀምሮ ነበር።


"ኢትዮጵያችን ካልተጠቀምችባቸው ብርቱ፣ ታሪክ አዋቂና ተመራማሪዎች መካከል ጋሽ አደም ባለ ከባድ ሚዛን የዲፕሎማሲ ሰው ናቸውና  ይታሰብበት" ያለው ነብዩ፣ "ጋሽ አደምን የመሳሰሉ በእውቀት የሚሰሩ ዜጎች ቢሰማሩ የሀገራችን ባህል በአግባቡ ተዋውቆ፣  የዜጎች መብት ተጠብቆ፣ ከአረብ ሀገራት የሚኖረን ትስስር ጎልብቶ የምናይበትን ጊዜ ቅርብ ያደርግልናል።"


ጋሽ አደም "ኢትዮጵያን እንደ ከህይዎቱ አብልጦ የሚወድ ፣ሲበዛ መልካም፣ የተቸገረን ደጋፊ፣ በመልካም ስብዕና የላቁ" ናቸው

Post a Comment

0 Comments