አገራችን ለሁሉም የምትበቃ ሁላችንንም የምታኖር ሰፊ እና ለምለም ምድር ናት‼️
የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ግን በጥቅምና በስልጣን ምኞትና ልክፍት የምስኪን ሰርቶ አዳሪ ዜጎችን ህይወት ቀን በቀን እንዲቀጠፍ ሲያደርጉ ኖረዋል አሁንም እያደረጉ ነው ። በቤኒሻንጉል ጉምዝ መተከል አካባቢ እና በኦሮሚያ ክልል የወለጋ አካባቢወች የሚሞቱ ወገኖቻችን ህይወት ምክንያቱ ሌላ ሳይሆን የእኛው የራሳችን ያልተገራ የፖለቲካ ፍላጎት እና የነዋይ እና ስልጣን ምኞት ነው ።
በዛሬው እለት በቤኒሻንጉል ክልል ጉምዝ ክልል በግልገል በለስ አካባቢ ተገኝተን ነፍስ አጥፊ ገዳዮችን እና ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ ባለው የመንግስት መዋቅር ግድያና እልቂት ሲያስፈፅሙ የነበሩ አመራሮች ላይ እርምጃ በመውሰድ በቁጥጥር ስር አውለን ወደ ህግ እንዲቀርቡ ከፍተኛ ስራወችን በመስራት ላይ እንገኛለን ። በዚህ እኩይ ድርጊት የተሳተፈ ባለስልጣን ይሁን የፓርቲ መሪ አልያም ወታደር ከህግ ተጠያቂነት አያመልጥም ።
ኢትዮጲያ በአዳዲስም ሆነ በቅሪት ጁንታወች አትደማም ፤ የአካባቢውን የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ በአጭር ቀናት ውስጥ አስተማማኝ በማድረግ የኢትዮጵያ ህዝብ እፎይ ብሎ የሰላም አየር የሚያገኝበት ቀን ሩቅ አይደለም ።
ሁላችንም ከሴራ ፣ ከአሉባልታ እና ከተንኮል ስጋት ወጥተን አንድ ሆነን አገራችንን ከፍ ማድረግ አለብን ።
#Via LG Bacha Debelle, Facebook page
1 Comments
best leader
ReplyDelete