#EUROPEAN_UNION‼️
በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና በሌሎች አካባቢዎች የሚፈጸሙ ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች እንዳሳሰቡት እና በገለልተኛ አካልም ሊጣሩ እንደሚገባቸው አውሮፓ ኅብረት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በጠቅላላው ሀገሪቱ የሚታዩት ጥቃቶች፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ ሰብዓዊ ቀውሶች እና ማንነት ላይ የተመሠረቱ ጥቃቶች አሳሳቢ ሆነዋል- ብሏል ኅብረቱ።
በትግራይ ክልል ያለው ግጭት እና ቀጠናዊ ተጽዕኖው ለዐለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ አሳሳቢ እየሆነ ያወሳው መግለጫው፣ ግጭቶች ሙሉ በሙሉ መቆም እንዳለባቸው፣ ዕርዳታ ለዕርዳታ ፈላጊዎች ያለ ምንም እክል እንዲዳረስ እና ሁሉም ወገኖች ዐለማቀፍ የሰብዓዊ ሕግጋትን ለከበሩ እንደሚገባ አሳስቧል።
ስደተኞችም ሆኑ ተፈናቃዮች ወደ ሀገራቸው ወይም ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እንዳይገደዱም ጠይቋል።
1 Comments
sad
ReplyDelete