የሙለር ሪልስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው አዲስ የምርመራ መዝገብ ተከፈተባቸው!


 የሙለር ሪልስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው አዲስ የምርመራ መዝገብ ተከፈተባቸው!


ተጠርጣሪው አዲስ በተከፈተባቸው የምርመራ መዝገብ በመጪው ሰኞ ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው ይታያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡


ከእርሳቸው ጋር የዋስትና መብታቸው የተከበረላቸው ኃይላይ መዝገበ እና ሳሙኤል አባዲ ላይ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ ይግባኝ መጠየቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡


ግለሰቦቹ የሕወሓት እና የኦነግ ሸኔ የጥፋት ቡድኖች የፋይናንስ ምንጭ ሆነዋል በሚል ወንጀል ተጠርጥረው ጉዳያቸው በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ሲታይ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ 

@sheger 24 media

Baby products

Post a Comment

1 Comments